Sunday 30 November 2014

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ የወጣቶች ክፍል አዘጋጅነት ታላቅ ሰላማዊሰልፍ በኖርዌይ ኦስሎ ተካሄደ!!!

Source : Abi A

  የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ሰላምና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ እንዲሰፍን በኖርዌይ የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውን የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት የተቋቋመ የድጋፍ ድርጅት ነው። ድርጅቱ ለዲሞክራሲ ግንባታና ለሰባዊ መብት መከበር ለሚታገሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች ድጋፍ ከመስጠቱም በተጨማሪ የወያኔን ኢ_ሰባዊና ኢ_ዲሞክራሲያዊ ድርጊት ማጋለጥና የወያኔ ባለስልጣናትን ማዋረድ ግንባር ቀደም ተግባሩ ነው።

በዛሬው እለት ማለትም ሀሙስ (November 27,2014)  በድርጅቱ የወጣቶች ክፍል አዘጋጅነት በኖርዌ ኦስሎ በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከሩቅም ከቅርብም በአንድነት በመሰባሰብ ከቀኑ 13፡00 እስከ 15፡00 ስዓት ታላቅ የተቃውሞ ድምጽ አሰሙ።

የተቃውሞው ዋና አላማ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ  በአንምባ ገነኑ የወያኔ ቡድን በህገ ወጥ መንገድ ታፍነውና ፍትህ ተነፍገው በእስር ቤት መታሰራቸውን ለመቃወም ነው። በተቃውሞው ስፍራ የተገኙ ሰዎች ሁሉ አቶ አንዳርጋቸው ለዲሞክራሲ እና ሰባዊ መብት መከበር ከወጣትነት ጀምሮ የታገለ ታላቅ የሰላም ምሳሌ፣ የፍትህ ተምሳሌት፣ የነጻነት በር ከፋች እንዲሁም አገራዊ ስሜት የተላበሰ አርበኛ እንጂ እስር፣ ድብደባና መሰቃየት የሚገባው ሰው አልነበረም በማለት ለእንግሊስ መንግስት በኢንባሲው አማካኝነት ዜጋዋን ከአረመኔና ጨካኝ መዳፍ እንድትታደግና ፍትህ እንዲያገኝ  በከፍተኛ ድምጽ አሳስበዋል።

ወጣቶች እጃቸውን በሰንሰለት በማሰር እኛም እንደ አርበኛ ው አንዳርጋቸው ጽጌና በእስር ቤት የሚሰቃዩ ኢትዮጵያውን የቁም እስረኞች ነን የሚል ጥልቅ መልእክት አስተላልፈዋል። ብዙ መስራትና መጻፍ የሚችሉ እጆች፣ መናገር የሚችል አንደበት፣ የእውቀት ባለቤት የሆነ አእምሮ ታስረዋልባ እኛም ወጣቶች እስረኞች ነን በሚል ውስጣዊ ስሜት ለስዓታት የኖርዌ ብርድና ቁር ሳይበግራቸው እጃቸውን በሰንሰለት አስረዋል።

እንዲሁም ሰልፈኞች የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ በታላቅ ድምጽና ስሜት ለኢንባሲው አሰምተዋል።  ከአሰሟቸው  መፈክሮች መካከል ለአብነትም “ Britin were is your citizen, Free Andrgachew Tsige, Andargachew is our icon of democracy, where is your action , stop discrimination among citizens, Yes, we are all Andrgachew Tsige, Brtain dont support terrirost regim in Ethiopia” የሚሉት ይገኙበታል::
ሰልፎኞችም የኢንግሊዝ  መንግሥት የነጻነት ታጋዩን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ከወያኔ እጅ እስካላወጡት ድረስ ተቃውሞው ቀጣይነትና ያላችውን ፍቅር በአደባባይ ያስመሰከሩ ሲሆን የተቃውሙ ሰልፉም በሰልፈኞቹ ቁጣና እልህ የተሞላአንዳርጋቸው ያላቸውን ክብርና ፍቅር እስከ መጨረሻው ድረስ ከዚህ በበለጠ ድምጻቸውን እንደሚያሰሙ ተናግረዋል።
በመጨረሻም በድርጅቱ የተዘጋጀውን  ደብዳቤ መድርጅቱ ሊቀመንበር በአቶ .........እና በሰልፉ አዘጋጅ ኮሚቴ የወጣቶች ተወካይ በወጣት ............አማካኝነት ለእንግሊዝ ኢምባሲ ተወካይ ጉዳዩ ትኩረት የሚሻና ጊዜ የማይሰጠው መሆኑን አሳስበው ደብዳቤውን አስረክበዋል። በመጨረሻም ሰልፈኞቹ በአንድ ላይ በመሆን የግንቦት 7 ህዝባዊ ኃይል መዝሙር ላንቺ ነው ሀገሬ ላንቺ ነው ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላንቺ ነው የሚለውን ህዝባዊ መዝሙር በደማቅና በሀገራዊ ስሜት ዘምረው ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ ከቀኑ 1500 ተጠናቋል።