Wednesday 23 January 2013

ምስጢራዊው የበረሃው ሲኖዶስና የማህበረ ቅዱሳን ፓትርያርክ፣ ከአብየ አዲ እስከ አዲስ አበባ


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን በተመለከት ÷ ለሰሚ የሚገርሙ ዜናዎች መሰማት ከተጀመረ ከርሟል :: ግን ቤተ ክርስትያኗ እንዲህ ትሆን ዘንድ ከበረሃ ጀምሮ የተጠነሰሰና የታቀደ ረቂቅ እቅድ መኖሩናን ÷ አሁንም እየተተገበረ ያለው ያ መሆኑን በርካታ ዜጎች ያወቁ አይመስልም:: ህወሀት በረሃ እያለ በ1980ዎቹ ውስጥ ፓትርያርክ እንዳዘጋጀ ስንቶቻችን እናውቅ ይሆን? ። ቤተ ክርስትያኗን እሰክወዲያኛው ለመቆጣጠር የህወሀት ካድሬዎች ጳጳሳት ሆነው የቤተ ክርስትያኒቱ ከፍተኛ መዋቅር ላይ እንዲቀመጡ ተደርጓል:: ሌላም ሌላም:: የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን በኢህአዴቅ ቅኝ ግዛት ውስጥ እንዴት እንደወደቀች በማስረጃ እንመልከት:: ነገርን ከስሩ ውሃን ከጥሩ ነውና ከመጀመርያው እንጀምር:: የመጀመርያው መጀመርያ::


መቻ ኦርቶዶክስ – ህወሀትና ለቤተ ክርስትያኗ የደገሰው የሞት ድግስ


የትግራይን ብሄርተኝነት (Tigray Ethnicism) አንግቦ የተነሳው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ÷ ይከተል የነበረው ርእዮተ ዓለም
( Marxism) ማርክሲዝም ሌኒንዝም ነበር:: ሲጀመር ማርክሲዝም ጸረ ሃይማኖትና ሃይማኖትን ማዋረድና ማራከስ ዓላማው የሆነ ፖለቲካዊ እሳቤ ነው:: ከዚያ ፍልስፍና በመነሳት ይሄ ድርጅት ታሪካዊቷን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን “ፊውዳልና መመታት ያለባት” አድርጎ ፈረጀ:: ሲቀጥል ደግሞ ህወሀት ብሄርተኛነት ( Ethnicity) ላይ እንጂ ብሄራዊነት ወይም አሀዳዊነት (Unitary) ወይም አንድነት ላይ ንቀት የነበረው ደርጅት ስለነበረ÷ ያገሪቱ አንድነትን የሚያንጸባርቁ ድርጅቶችን በሙሉ እንደጠላት የማየት አባዜ የነበረበትና አሁንም ያለበት ድርጅት ነው::


ቤተክርስትያን ደግሞ ሕብረ ብሔራዊት መሆኗ ህወሀት ጥርስ ውስጥ ለመግባት በቂ ምክንያት ነበር:: ይህንንም የሕወሀት መስራችና የቀድሞ መሪ የነበሩት ዶክተር አረጋዊ በርሄ A Political History of the Tigray People’s Liberation Front (1975-1991): Revolt, Ideology and Mobilization in Ethiopia በሚለው ለዶክትሬት ማሟያ በጻፉ ድርሳናቸው ውስጥ እንዲህ ሲሉ በማያወላዳ ቋንቋ ገልጸውታል


The pragmatic TPLF understood the church’s role in village social life and its support for the unity of the country. It also understood a possible alliance between the Church with forces that stood against socialism and nationalization of the land as well as against separatism. The church was viewed as a force standing in the way of the TPLF but one that should be handled with caution. .. There was no doubt that that it wanted to subordinate the church to its cause .ይህንንም ዓላማ ዳር ለማድረስ የተመቀበት መሰሪ ዘዴ
 

1ኛ የቤተ ክርስትያን ሰው መስሎ አብያተ ክርስትያናቱ ውስጥ መሰግሰግ÷

2ኛ በትልልቅ ገዳማት÷ መነኮሳትንና ካህናትን በማሳሳት ለሕወሀት ጸረ ቤተ ክርስትያን ዓላማ ተገዢ ማድረግና

3ኛ ለዘለቄታው ቤተ ክርስትያኗን ለማሽመድመድና በቁጥጥሩ ስር ለማስገባት የራሱን ካድሬዎች ሲኖዶስና ከፍተኛ አመራር ውስጥ
በማስገባት ሙሉ በሙሉ ቤተ ክርስትያኗን መቆጣጠር ነው:: እያንዳንዱን በደጋፊ መረጃ እንመልከት


የሀወሀት ካድሬዎች ገዳም መግባት


የህወሀትን ታሪክ ከጻፉት ጥቂት ሰዎች መካከል ለአሜሪካ የመረጃ ድርጅት ቅርበት እንዳላቸው የሚታመነው John Young, Peasant Revolution in Ethiopia: The Tigray people Liberation Front ( 1975- 1991) በሚለው መጽሀፋቸው ገጽ 176 ላይ የሕወሀት ካድሬዎች ላሰቡት ስውር ዓላማቸው እንዲረዳቸው የቤተ ክርስትያንኗን ትምህርት ማጥናት እንደጀመሩ እንዲህ ሲሉ ይገልጹታል


“TPLF cadres spent considerable time studying the Bible and the teaching of the church so as to equip themselves for the task


እነዚሁ በዓላማ የቤተክርስትያኗን ትምህርት እንዲያጠኑና መነኩሴ እንዲመስሉ የሰለጠኑት የህወሀት ካድሬዋች በአቶ ስብሀት ነጋ በሚመራ የስለላ መዋቅር በየገዳማቱ እንዲበተኑ እንደተደረገና ÷እነዚህም ሰላይ የድርጅት አባላት የየገዳማቱን ቁልፍ ቦታ እንዲይዙና መንፈሰ ልል መነኮሳትን እንዲመለምሉ መደረጉን ሁኔታውን ባይናቸው ያዩትና ÷ በወቅቱ ይድርጅቱ ሰብሳቢ የነበሩት ያሁኑ ዶክተር አረጋዊ በርሄ እንዲህ ሲሉ ነበር ያስቀመጡት


This process involved the mobilization of parish priests and ordinary Christians to isolate them from the church’s national hierarchy. To weaken church authority, an intelligence group was formed under Sibhat Nega to infiltrate the well-established monasteries in Tigrai, such as Debre Damo, by planting TPLF members camouflaged as monks and influencing church activities in the interests of the TPLF.


የጭቁን ካህናትና ሰላይ መነኮሳት መፈጠር


የቤተ ክርስትያንን ትምህርት አጥንተው ÷ የቤተ ክርስትያን ሰው መስለው ወደየገዳማቱ በመሄድ ስልጣን የተቆናጠጡት መልክተኞች ቀስ በቀስ የአብያተ ክርስትያናቱንና የገዳማቱን ማህበረሰ ማሽከርከር ጀመሩ:: የተቃወሟቸውን አባቶች በማስገደልና በማሳፈን ሌሎቹንም በተለያየ ሁኔታ በማምታታት ባጭር ግዜያት ውስጥ በርካታ ገዳማትና ትልልቅ አብያተ ክርስትያናት የህወሀት መጋለቢያ ምቹ ሜዳዎች ሆኑ::


ጥቂቶችን ካህናትን የሃይማኖቱ ህግ ከሚፈቅደው ውጭ ጠመንጃ በማስታጠቅ ታጋይ ቀሳውስት ሲያደርጓቸው ሌሎቹን ደግሞ የስለላ መዋቅር ውስጥ በመሰግሰግ በተሳካ ሁኔታ ተዋጊ ካህናትና ሰላይ መኮነሳትን ለመፍጠር ቻሉ::ይህንኑ ጉዳይ አጥብቆ የተመራመረው አሜሪካዊው ምሁርና የፖለቲካ ተንታኝ ፒተር ያንግ ይሄን የካድሬ ካህናት ጉዳይ በሰፊው እንዲ ሲል ከመጀመርያው አሳስቦ ነበር


Some priests rejected the church’s prohibition against taking up arms and became TPLF fighters, but most were too old to keep up with the youthful fighters and were more likely to join local militias or serve as teachers in front established schools. … Some priests played an important role in introducing fighters to other priests and local people in recently liberated territories. Such priests told people that unlike the atheistic Derg, the TPLF was made up of true Christians


Other priests assumed a similar role outside Tigray. Two such priests… reported that they served in the TPLF for seventeen years as political cadres , not carrying guns, but “agitating people” throughout newly liberated territories in Tigray and beyond to Gondar and Wello, as the Front took the struggle south in the final stages of the war. Since Amharigna and geez were the languages of the church they could be effectively employed throughout northern Ethiopia by the priests. Following the TPLF, these ambassadors–priests held meetings where fighters would be introduced to the priests of newly liberated territories as their “children” and always the contrast was made between the TPLF who came as liberators and the “atheist Derg”. Older and respected priests would then be recruited from each area to carry the word forth.


የበረሃው ቤተ ክህነትና የጫካው ሲኖዶስ ምስረታ


ቀስ በቀስ እነዚህ ታጣቂ ቀሳውስትና “ጭቁን ነን” ባይ መንኮሳቶች የስራ አድማሳቸው እየሰፋ መጣ:: ቁጥራቸው እየደገና እየተበራከተ መምጣቱን የተረዱት እነዚሁ አካላት ባካባቢያቸው ያሉትን አድባራትና ገዳማት ከመቆጣጠር አልፈው የቤተ ክርስትያን ቀኖናን መደንገግ ጀመሩ:: ክጥቂት ግዜያትም በኋላ የጫካውን ቤተ ክህነትና ሲኖዶስ ለመመስረት ቻሉ::


These conferences held near Abi Adi in 1983 and Roba kazi in 1984 did much to consolidate TPLF support from priesthood . Some 747 priests attended the first conference and 550 priests attended the second , at which delegates agreed to … . Significantly in the liberated territories , thus giving rise to a “TPLF secretariat” and a “ Derg Secretariat” which continued to function out of Mekele when Mekele was captured by the TPLF in 1989 the” Derg supported” Tigrayan secretariat was transferred to Wello., and the TPLF – supported secretariat assumed responsibility for the administration of the whole Tigray.


ይሄም የበረሃ ቤተ ክህነትና ሲኖዶስ ሀወሀት መቀሌን ሲቆጣጠር መንበሩን መቀሌ ላይ በማደርግ ” ነጻ የወጡ” አካባቢዎች ቤተ ክህነት መምራት ጀመረ:: ያዲስ አበባው የመቀሌ ሀገረ ስብከት ደግሞ ወደ ደሴ በመሸሽ መንበሩን ደሴ ላይ ተክሎ ግልጋሎቱን ቀጠለ:: ደሴ በህወሀት ሲያዝ ደግሞ ደሴ ቢሮ ከፍቶ የነበረው የትግራይ ሀገረ ስብከት ወደ አዲስ አበባ ሲሸሽ የጫካው ቤተ ክሀነት ደግሞ ደሴ ላይ ስሩን ተከለ:: ሀወሀት እየገፋም መጥቶ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ይሄው የጫካው ቤተ ክህነት አብሮ አዲስ አበባ ገባ:: የጫካው ቤተ ክህነት ግን የራሱን ፓትርያርክ መርጦ ጨርሶ ነበርና ቀጣይ ስራው ከተሾሙ ሶስት አመት ያልሞላቸውን ፓትርያርክ መርቆርዮስንና መሰል አባቶችን ቦታ ማስለቀቅ ነበር::


የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ጸሀፊ የነበሩት ሌንጮ ለታም ሕወሀት ገና ጫካ እያለ ሲኖዶስና ቤተ ክህነት መመስረቱን አልፎ ተርፎም ደግሞ ጳጳስ አዘጋጅቶ እንደነበረ The Ethiopian State at the crossroads በሚለው መጽሀፋቸው ላይ ለዓለሙ ማህበረሰብ እንዲህ በማለት ገልጸው ነበር.


Despite the fact that TPLF was an avowed Marxist –Leninist organization, it was engaged in conducting conferences in Tigrean clergy in the latter part of 1980s. One possible aim was to explore the selection of a new Patriarch or Abuna… What is of importance of the issue that we are dealing with is that an attempt was being made to create a new kind of relationship between the emerging authority and the institution of the church. The observable result was the emergence of a new kind of priest in TPLF held areas. A “militant priest” was supposedly fashioned in the process, as distinct from the priest that still continued to stay “ in the service’ of the regime.


የአቡነ ጳውሎስ ሹመትና የቤተ ክሀነቱ ባዲስ የሰው ሃይል መተካት


መርቆርዮስ ፓትርያርክ በሆኑ በሶስት አመታቸው ” በህመም ምክንያት” በሚል ከስልጣን ወርደው አቡነ ጳውሎስ ስልጣኑን ተቆጣጠሩት:: ከሳቸውም ስልጣን መያዝ ጋር ተያይዞ በርካታ አዳዲስ ” ካህናትና መነኮሳት” የቤተ ክህነቱ ሹመኞች ሆኑ:: በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ታይቶ በማይታውቅ መልኩም ÷ አቡነ ጳውሎስ አዳዲስና ወጣት ጳጳሳትን መሾም ቀጠሉ:: መረጃዎች እንደሚያሳዮት አቡነ ጳውሎስ በህይወታቸው እያሉ ከ 40 በላይ ጳጳሳትን ሾመዋል:: ይሄም በሁለት ሺህ አመት የቤተ ክርስትያን ታሪኳ ውስጥ ታይቶና ተሰማቶ የማይታወቅ ቁጥር ነበር:: በመሰረቱ የጳጳሳት በብዛት መሾም በራሱ እንደ ችግር ላይታይ ይችላል:: ነገር ግን ባቡነ ጳውሎስ የተሾሙት ጳጳሳት አብዛኞቹ ” የበረሃው ሲኖዶስ አባላትና የህወሀት ስራ አስፈጻሚ “ሲሆኑ አላማቸውም ለመንፈሳዊው ጉዳይ ሳይሆን ፓለቲካ ዘመም ነበር :: ይህም በተለያዩ ግዜያት በተካሄዱ የሲኖዶስ ስብሰባዎች ታይቷል::


አሁንም እንደሚታየው የአዲስ አበባው ሲኖዶስ ተከፋፍሏል:: ክፍፍሉም የሚታየው ነባሮቹ ጳጳሳትና አዲስ በተሾሙት ጳጳሳት መካከል ነው:: ነባሮቹ “ከፓትርያርክ ምርጫ በፊት እርቁ ይቅደም” ሲሉ አዲሶቹ ” ባስቸኳይ ሌላ ፓትርያርክ ይመረጥ ” የሚል የሃሳብ ጽንፍ ይዘው እየተሟገቱ ሰንብተዋል:: በቁጥር አብላጫውን የያዙት አዲሶቹ ያባ ጳውሎስ ጳጳሳትና የበረሃው ሲኖዶ ምልምሎች ሲኖዶሱን እየተቆጣጣሩት ብቻ ሳይሆን : በፍጹም ከቤተ ክርስትያን ተሰምቶ የማያውቅ ድምድ እያሰሙ ነው:: በስብሰባው ላይ አንዱ የበረሃ ጳጳስ ያለ ሃፍረት እንዲህ ሲሉ ነበር የተናገሩት”ፓትርያርክ መርቆርዮስ የሚመለሱ ከሆነ ትግራይ የራሷን ፓትርያርክ ትሾማለች”:: እንግዲህ ጳጳሳት በመሆን በአቡነ ጳውሎስ ተሹመው ቤተ ሲኖዶሱን የተቀላቀሉት እንዲህ አይነት አባቶች ናቸው::የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን እንዲህ አይነት አደገኛ አጣብቂኝ ውስጥ ገብታለች::የህወሀት አምባሳደርና ካድሬዎች የነበሩ መነኮሳት ሲኖዶሱን እየተቆጣጠሩትና ሲኖዶሱንም የፖለቲከኞች ስራ ማስፈጸሚያ እያደረጉት ነው::


የማህበረ ቅዱሳን ፓትርያርክ


የሴራው መሀንዲሶች ይሄን እኩይ ስራቸውን ለመሸፈንና ራሳቸውን ከደሙ ንጹህ ለማሰመሰል በርካታ ማጭበርበርያዎችን ሲጠቀሙ ቆይተዋል:: ከዚህም አንዱ “ማሀበረ ቅዱሳን የራሱን ፓትርያርክ ሊያሰመርጥ እየተሯሯጠ” እንደሆነ ማስወራትና ሕዝቡን ለማደናገር መሞከር ነው::ይሄም አላማው ሁለት ነው:: ባንድ በኩል ማህበረ ቅዱሳንን በሕዝቡ ለማሰጠላት ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የፓትርያርክ ሹመት ሽኩቻው ውስጥ መንግስት እጁ እንደሌለበትና መተራመሱ ያለው የተለያየ አላማ ባላቸው የቤተ ክርስትያኗ አካል እንደሆነ ለማስመሰል ነው:: ይሄንንም ከዳር ለማድረስ በተለይ ወያኔ በውጭው ዓለም ያሰማራቸው ሰላይና ቅጥረኛ ጸሀፊዎቹ ” ከፓትርያርክ ሽኩቻውና እርቀ ሰላሙ አለመሳካት ጀርባ ማሀበረ ቅዱሳን መኖሩንና ዓላማውም የራሱን ፓትርያርክ ማስመረጥ” እንደሆነ ጆሮ አደንቁር የሆነ ጽሁፍ በማውጣት የወተቱ ጠቆረ ማሩ መረረ ዘመቻውን አፋፍመውት ከርመዋል- የሚሰማቸውና የሚያምናቸው ባይኖርም::


ሌላ የጨለማና የውዝግብ ዘመን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን


የፓለቲካውን ጉዳይ ለማስፈጸም እንጂ ለቤተ ክርስትያኗ እድገት ብዙም ደንታ ባልነበራቸው በአቡነ ጳውሎስ ዘመን ቤተ ክርስትያኗ የተከታዮቿን ሰባት ፐርሰንት አጥታለች:: በቀረውም ምእመን ላይም ከባድ የሞራል የስነ አእምሮና ባባቶች ላይ ተስፋ የማጣት ሁኔታ ተከስቷል:: ተጀምሮ የነበረው እርቀ ሰላምም መክሸፉ የብዙዎችን ልብ ሰብሯል:: ከሁሉም በላይ አሳሳቢው ግን አሁንም ቀጣይ የሚመረጡት ፓትርያርክ ጉዳይና ሁለቱም ሲኖዶስች ውስጥ እየታየ ያለው ሃይማኖትን የመገዝገዝ አባዜ ነው::


የውጭው ሲኖዶስ በቤተ ክርስትያኗ የሀይማኖት ህጸጽ ( ስህተትና ኑፋቄ) ተገኝቶባቸው ከቤተ ክርስትያን ተለይተው የነብሩ መናፍቅ ሰባክያንን በማወቅም ይሁን ጡንቻ ለማጠንከር እያስጠጋቸው ነው:: አልፎ ተርፎም የቤተ ክርስትያን አስተዳዳሪ ሲሆኑ እየታየ ነው:: ከዚህም አልፎ የውጭው ሲኖዶስ በሚያስተዳድራቸው አብያተ ክርስትያናት ውስጥ ” ዘመኑን ለመዋጀት ” በሚል ሽፋን በቤተ ክርስትያኗ ቀኖና ጥቅም ላይ እንዳይውሉ የተደነገጉ እነ ኦርጋንና ፒያኖን የመሰሉ መሳርያዎች ገብተው የአምልኮውን መልክ እየቀየሩት ነው:: የአዲስ አበባውም ሲኖዶስ የመንግስት under cover agents የሆኑ ጳጳሳት ተሰግስገውበታል:: እነዚም ወገኖች ዓላማቸው የፖለቲካውን አጀንዳ ማስፈጽም እንጂ ሃይማኖት ባለመሆኑ ለቤተ ክርስትያኗም ሆነ ለመንጋው ደንታ የሌላቸው ጨካኞች ናቸው:: ቤተ ክርስትያኗ ከሁለት ወገን ተንጋላ እየታረደች ነው::

 
ለዚህ ሁሉ መሰረት የሆነውን ችግር ታላቁ ካናዳዊው ተመራማሪ ፕሮፌሰር ቴዎዶር ቬስቴል ይህንን ጉዳይ እንዲህ ሲሉ ነበር ያስቀመጡት.This and other acts of violence in and around churches have alienated the Patriarch from his spiritual flock and have contributed to the EPRDF goal of exploiting internal contradiction with in the EOC leadership to weaken any opposition to the front.


ግን ወያኔ ለዘላለም ይኖር ይሆንን? የቤተ ክርስትያን አምላክ ሆይ ቤትን አጽዳ!
ማጣቀሻ መጻሕፍት

No comments:

Post a Comment