Sunday, 9 March 2014

አቶ ኦባንግ ሜቶ እና አቶ አብዱላሂ ሁሴን በኖርዌይ ኦስሎ ከኢትዮጵያውያንና ከኖርዌጅያን ባለስልጣናት ጋር ተወያዩ


Source AbiAmare

አቶ ኦባንግ ሜቶ የአዲሲትዋ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ፓሬዝዳንትና አቶ አብዱላሂ ሁሴን  የኦጋዴን ክልል ፕሬዝዳንት አማካሪ የነበሩና በክልሉ የሚደረገውን የህዝብ ጭቆና፥ እንግልት፥ ግድያ  የሚያሳዪ ወደ መቶ ሰአታት የሚደርሱ የቪዲዮ ማስረጃዎችን ይዘው በመሰደድ ለአለም ህዝብ እያጋለጡ ያሉና በአሁኑ ሰአት በስዊድን ሃገር የፖለቲካ ጥገኝነት አጊንተው የሚኖሩ ሲሆን ከማርች 6 እስከ ማርች 7 ,2014 በነበራቸው የኖርዌይ ቆይታቸው ከተለያዩ የኖርዌይ ባለስልጣናት ጋር በሃገራችን ውስጥ ስለሚደረገው የሰብአዊ መብት ረገጣ በማስረጃ በተደገፈ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፥ በመቀጠልም በነበራቸው ቆይታ ስፖንሰር አድርገው ባመጧቸው Solveig Syversen በተባሉ አክቲቪስትና እንዲሁም  Frontline Club Oslo በተሰኘ ድርጅት በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኖርዌጂያንና ኢትዮጵያውያን Filmenshus በተባለ ቦታ ተገኝተው በኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በማስረጃ በተደገፈ ለህዝብ ያቀረቡ ሲሆን ከታዳሚውም በተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን፥
                                      
 
                        
ማርች 7/2014 የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አጋጣሚውን በመጠቀም በጠራው አስቸኴይ ስብሰባ አቶ ኦባን ሜቶ እና አቶ አብዱላሂ ሁሴን ከኢትዮጵያውያኑ ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ያረጉ ሲሆን በቀጣይም በሃገራችን እየተደረገ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት፥ ግድያ፥ እስራት ለማስቆም ምን መሰራት አለበት በሚሉት አንገብጋቢ ነጥቦች ዙሪያ ከታዳሚውም ከእንግዶቹም የተለያዩ ሃሳቦች ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ አቶ አብዱላሂ ሲያጠቃልሉ ያለብንን ችግር ለመፍታት የርስ በርስ ሽኩቻችንን ትተን ትኩረታችንን ሃገራችንን እያመሰ ያለው የወያኔ መንግስት ላይ እናርግ በማለት ምክራቸውን የለገሱ ሲሆን አቶ ኦባን በበኩላቸው እነዚህ በአቶ አብዱላሂ ሁሴን ከሃገር የወጡት ማስረጃዎች በጣም ተቃሚ ማስረጃዎቻችን እንደሆኑና ወደፊት ጊዜው ሲደርስ መጠየቅ ያለባቸው አካላት ሃላፊነት እንደሚወስዱበት ጠቁመው ነፃነታችንን ለማስመለስ ሁላችንም መታገል እንዳለብንና የውጩ አለም እኛን ነፃ ያወጣናል ብለን ዝም ብለን መቀመጥ እንደሌለብን ያሳሰቡ ሲሆን፥ በመጨረሻም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ዋና / አቶ ዮሃንስ አለሙ ለታዳሚዎችንና ለእንግዶቹ  ምስጋና በማቅረብ በአጭር ግዜ በተጠራ የውይይት መድረክ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን መገኘታቸውን አድንቀው ለቀጣይ በጋራ ሊሰሩ ስለሚችሉ ስራዎች ግኑኝነት እንደሚቀጥልና ድርጅታቸውም በማንኛውም ስራ ላይ በግንባር ቀደምነት በሩን ከፍቶ እንደሚጠብቅ ገልፀው ስብሰባው ተጠናቋል፥፥



No comments:

Post a Comment