Tuesday, 12 February 2013

Patriotic Ethiopians in Sweden and Norway accord human rights activist Tamagn Beyene a hero's welcome!

 
  
 


 
                                   

ESAT  FUNDRAISING COMPAINGN OF  10 feb 2013 NORWAY

all Ethiopians in Norway who participate supporting ESAT fundraising in a way you can.I personally learn from this fundraising event that unity is strength & success & we can make a change & Hoping that our unity working together will continue ! ESAT Fundraising in Norway for 2013 was the Best! 




1 comment:

  1. አማራነት ኢትዮጵያዊነት ነው!
    እውቅና ለሚገባው እውቅና ለመስጠትና ለማመስገን አንፍራ፡አንፈር ከኛ የተሻለ ለሰሩና ለደከሙ እወቅና መስጠትና ማበረታታተ የተሻለእንዲሰሩና አርአያ ሆነው እንዲቀጥሉ የደርጋል፡፡ለእኛም ቢሆን ጠንካራ ጎንን ማድነቅና ማበረታታት ለራሳችን ያለንን ግንዛቤም የሚያሳይ በመሆኑ ታላቅነትን ለማድነቅ ጭራ አነሁን፡፡ ለምሳሌ ኢትዮጵያዊነት ሲነሳ ከፊት የሚቀድመውና በጣም ጎልቶ የሚታየው አማርኛ ቋንቋችን ነው፡፡አማርኛ የራሳቸው ፊደልና መቁጠሪያ ካላቸው በጣም ጥቂት አገራት አንዱ ሲሆን ለአፍሪካም አንድ ለናቱ የሆነ የኢትዮጵያዊነት ቁንጮና ክብር ነው፡፡ ለዚህ ነው አማራነት ኢትዮጵያዊነት አንጂ ብሄረተኝነት አይደለም የሚባለው፡፡ዜግነት መለካት ያለበት በትንሽ የብሄርተኝነትና የጎጠኝነት መስፈሪያ ሳይሆን፤በራሱ በኢትዮጵያዊነት መሆንና መታየት ይገባዋል የሚባለውም ለዚያ ነው፡፡ከዚህ አንጻር እኔን ያልደገፈ ሁሉ ጠላቴ ነው ከሚል ፤ዜግነት እኔን የተከተለና የደገፈ ማለት ነው ከሚል የቂምና የጥላቻ ሰይጣናዊ መንገድ ወጥተን ዜጋ ነጻ ሆኖ መኖር የሚችልባት፡ዜጋ የሚጠቀመውም የሚጎዳውም በደጋፊነት ሳይሆን በስራውና በድካሙ ብቻ የሆነባት አገር፡ነጻ ሆኖ መኖር የፈለገ ሳይገለልና ሳይሸማቅ ከጠላትነት ሳይፈረጅ የሚኖርባት አባቶቻችን በመስዋእትነት ያወረሱንን የነጻነት አገር በነጻነት ልንኖርባት ይገባናል፡፡የዜግነት መስፈርቱ ራሱ ኢትዮጰያዊነት ብቻ እንጂ የመደገፍና የመቃወም ጉዳይ መሆን የለበትም፡፡ ኢትዮጵያዊነትን የሚመጥነው ነጻ ሆኖ ማሰብና በነጻነት መኖር ነው፡ይህንንም ያቆዩንና ያወረሱንን ጀግኖች አባቶቻችንን ልናመሰግንና ልናከብራቸው ግድ ይለናል፡፡እነሱ፡- በልቶ መኖርን ብቻ ሳይሆን ታምኖ መሞትንም፡የናጻነት ትርጉም እስከምን ደረስ እንደሆነ ለአለም ያስተማሩ ጀግኖች፤በእምነትም በኩል በቁስና በታይታ ወደውጭ ከመኖር ባለፈ ቅጠል ቀንጥበው ጤዛ ልሰው አለምን በመናቅ ወደውስጥ እየኖሩ እምነትን ያቆዩን የእምነት አርበኞች ናቸው፡፡ ለእነሱ ሁሉም ነገር ከኢትዮጵያዊነት በመለስ ነው፡፡ኢትዮጵያዊነት ቀይ መስመር ነው፡፡ ኢትዮጵያዊነትን ለማቆየት በጎራዴና ጋሻ ታንክና መትረየስን መክተዋል፤በህይወት መስዋእትነት የእሳት ላንቃ አጥፍተዋል፡፡ ስለዚህ በማንኛውም መንገድ ለሃገርና ለኢትዮጵያዊነት ለደከሙ እውቅና መስጠት ተገቢ ነገር ነው፡፡ በእነዚህኛዎቹ (በዘመነኞቹ)ግን፡- -አጀንዳቸው በግለሰብ፡በአካባቢና በጎሳ ላይ ለተመሰረተ ስለሆነ የ30 እና የ50 አመት እቅድ የላቸውም፡አገርን በመሸጥ ከሚያገኙት ቢሊዮን ዶላር በመቀንጨብ እየሰሩ በማፍረስ ለሚጫወቱት ልማት ለሚሉት ነገር እንኳን የራሳቸው ስም መጠሪያና ማስታወቂያ ብቻ ነው ብዙ አጠራጣሪና በታሪክም ፊት ምህረት የሌለው አጠያያቂና አሳፋሪ እውነታዎች በጉልህ እየታዩ ናቸው፡፡ኢትዮጵያዊነትን እንደጦር የሚፈሩ፤ህልውናቸው በኢትዮጵያዊነት ኪሳራ ላይ ብቻ የተመሰረተ፡መለያየትን፡ቂምና ጥላቻን ዘርተው በማጨድ በእንክርዳድ የሚበለጽጉ ህቡአን ናቸው፡፡ መገለጫቸው፡- -ሁሉም ነገር የህልውናቸው መሰረት ነው፤ደጋፊ እንጂ መሃል ሰፋሪና ተቀነቃኝ የሚባል ነገር አይታወቅም፤ደጋፊ ያልሆነ ሁሉ ጠላት ስለሆነ በጥርጣሬና በአይነ ቁራኛ ከመታየት አያመልጥም፤ የህልውና ጥያቄ ስላለበት ሁሉ ነገር ስውር አጀንዳና አጠራጣሪ ነው፡በግድ የሚጫን እንጂ ተማምኖ መሄድ የሚባል ነገር የለም፤ -የኢትዮጵያዊነት ጥያቄን በማሳነስ ቢቻል በማጥፋት ልዩነትን ማጉላት :ልዩነቱንም ለመፍጠር ከግለሰብ እስከ ሃገር፡ከፖለቲካ እስከ ሃይማኖት ተቋማት ድረሰ ማስፋት ነው፡፡ -በመስዋእትነት ታፍራና ተከብራ የኖረችን አገር በመቆራረስ ለዚያም ለዚያም በማከፋፈል እንደጠላት ገንዘብ በማድፋፋት ባለቤቱን በድህነት እንዲኖር የማድረግ የበቀል ተግባር መፈፀም ነው፡፡ ለዚህ ነው አሁን አሁን አየተፃፉ ያሉ አንዳንድ የታሪክ መፃህፍት ነን ባዮች ምንጫቸው ከዚሁ ሰይጣናዊ መንፈስ የተቀዱ በመሆናቸው እናት ኢትዮጵያን በማሳነስና ዝቅ በማድረግ ኢትዮጵያዊ ማንነትን አጥፍተው ፡እነሱ አገር ሸጠው ካገኙት እርጥባን ጠብ በማድረግ፡ ቀና ብሎ የማያይ ለእለት እንጀራው ሲል ብቻ የሚኖር ጥገኛ ዜጋ እና እንደፈለጉት የሚነዱትን ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተጉ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ነገርን ከምንጩ፡ችግርን በእንጭጩ ነውና ኢትዮጵያዊነት የሚገደን ሁሉ ልናስብበት የሚገባ ጉዳይ ነው እላለሁ፡፡

    ReplyDelete